October 19, 2026

ነገሮች በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው። Mesay Mekonnen ( From Facebook)

0

አብይ አህመድ ከማዶ ሲያማትር የትብብር ሃይሉ እግሩ ስር ከቤተመንግስቱ ደጃፍ ተጠግተዋል። ጦርነቱን መሀል አዲስ አበባ አድርገውታል። ብልጽግናዎች ስለመቀሌ መያዝ አሰፍስፈው ሲጠብቁ አዲስ አበባ ከእጃቸው ልትነጠቅ መሆኑን ምልክቶች እየታዩ ነው። አስደናቂ ነገሮች በአይናችን ስር እየሆኑ ነው። የማታው ፍንዳታዎች ቅምሻ ናቸው ብለዋል ከትብብር ሃይሉ መረጃ የሚቃርሙ ምንጮች። ምናልባት ከሰሞኑም አስደማሚ ክስተቶችን እንታዘባለን – አብይ አህመድ መሬቱንም ሰማዩንም የሚነጥቀው ‘ጠላት’ አፍንጫው ስር እየተንጎማለለ ነው ሲሉም አክለውልኛል። እንግዲህ ታሪክን በልኩ ሲሰራ እኛም ለመጻፍና ለትውልድ ለማስቅረት እንተጋለን። አዲስ አበባውያን ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋችኋል። የቆሰለ ጅብ የሚያደርገውን አያውቅም። በየህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፥ የገበያ ማዕከላት ላይ አገዛዙ ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል ከብሄራዊ መረጃና ደህንንነት አከባቢ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን መረጃውን ሹክ ብለውናል። ጥንቃቄ ..ጥንቃቄ..ጥንቃቄ..
በነገራችን ላይ እነጃዋርም በይፋ ብልጽግና መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገረ መንግስቱን ለማዳን ስንል ከብልጽግና ጋር እንሰራለን ብሏል ጃዋር ቃል በቃል። እንዲህ ነው ወንድም ጃዋር። ጎበዝ። ደጋፊዎችህን እኮ ልባቸውን ዝቅ አድርገህ ልትገላቸው ነበር። እንዲህ እውነቱን ነግረሃቸው ትንሽ እረፍት ያግኙ። ላንተም መወዛወዙ አልጠቀመህም። ወዲህና ወዲያ ስታማትር አንገትህን ስትራፖ ቆልምሞት ስትሰቃይ አየንህ እኮ?! እርፍ በል እንግዲህ።
የማነህ ይሉኛል፥ የማን ልበላቸው፥
የአብይ የበሸሻው ብለህ ንገራቸው
ተቀበል እንግዲህ?! ማነህ አዝማሪው ግጥሙን ድገመው እስኪ። ለማንኛውም ለውጡ ከሚጠበቀው በላይ እየፈጠነ ነው። ፕ/ር መሀመድ ሀሰን ”አሁን ሻንጣችሁን ማዘጋጀት ጀምሩ” ያለው ምን ታይቶት ይሆን?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish