መልስ፣ ለፍሬሰናይ ከበደ ገብረየስ“ ከባሕር ሓይላችን ታሪክ” የተከበርክ ጓድ ባሕር ሃይል ነበር !
ጽሁፍህን በተደጋጋሚ አንብቤው፣ ምንም አይነት ቁምነገር ላገኝ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም፣
ጥላቻ የሞላበት፣ ዛቻ የበዛበት፣ ከሱም አልፎ በጠባብና በባላባታዊ የድሮ የአማራ ትምክህት የተሞላና፣ እግረመንገዱም
ከተቻለ፣ ምጽዋ ቶሪኖ ሆቴል ላይ፣ ዱክ ብሎ ቢራ እየተጎኖጩ፣ ቆንጆ ኤርትራዊት ሴት ብሳንጃና በሽጉጥ አስፈራርቶ
እንደገና የመንደላቀቅ አጉል ህልም ያካተተም ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ከወዲሁ ብውሸትናብጉራ የተካነ፣ የኤርትራ
ነጻነትና ክብር የሚዳፈር፣ ከዛ አልፎም የኤርትራ ጀግኖችን የሚያንቋሽሽ አስነዋሪ ጽሁፍ ነው፡፡ ከመጀምርያ እስከመጨረሻ፣ በወንበዴ ጀምሮ በወንበዴ የሚያልቅ፣ አደገኛና፣በኢትዮጵያዊያንንና በኤርትራውያን ማሃከል የሚፈለገው ዘላቂ ወንድማማችነትና ጓደኝነትም የሚጻረር ጽሁፍ ነው፡፡ ከወዲሁ ልነግርህ እምወደው፣ ጊዜ ያለፈበት ( Stereotype)፣ ቅንብር ያጣና ታሪክ የተፋው ጽሁፍ ነው ብልህ ድፍረት አይሁኑብኝ፡፡ የድሮ ጠባሳና ቂም-በቀላዊ ስሜት እየታከመበት ባለው በአሁኑ ወቅት፣በዕድሜ ከገፉትና እንዳእንተ ከመሰሉት መራራው የኢትዮ-ኤርትራ ደም መፋሰስን ሊመሰክሩ ከሚገባቸው
የዕድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያውያን እንዲህ አይነቱ አደገኛና ትምክህተኛ ጽሁፍ መጻፍ
አይገባውም፡፡ ይሁን እንጂ ተገቢውን መልስ ይሰጥህ ዘንድ፣ የኛ የኤርትራውያን ሚናና ሃላፊነት ነው፡፡ ለዚህም ነው፣
ረጋ ብለህ የምታነበው መልስ ልጽፍልህ፣ ብዕሬን ያዋደድትኩት፡፡ እርግጠኛ ነኝ ባሁኑ ሰዓት ወደ ጥሮታ ገደማ
እየነጎድክ ነው፡፡ ጽሁፍህ እንደሚያሳየው / እንደምያትተው ደግሞ፣ ከመሞትህ በፊት ያጤንከው ፣ ያ የተለመደው
ባላባታዊና ገባች አስተሳሰብ፣ ባዲሱ የኢትዮጲያ ወጣት ትውልድ ለማስረጽ ‘የአልሞት ባይ ተጋዳይ’ ሙከራህ ነው፡፡
ቢሆንም ቅሉ፣ የምንኖርበት ዘመን በጣም የተለየ ዘመን ነው፡፡ ንብረት ለባለ ንብረቱ ፣ ታሪክ ለባለ ታሪኩ ፣እውነት ደግሞ፣በሃቅ ለሚታገሉና ለሚጥሩ ሃይሎች ነው የሚገባው ይላል፡፡ ለዚሁ ነው ያ ያለፍትህ፣በአመሪካ ወረተኝነት አባቶችህ የገበቱት የኤርትራ ባሕር ( ባሕረ-ኤርትራ) ለባለቤቶችና ለባለታሪኮቹ ብትግልና በህግ የተመለሰው፡፡ ባይገርምህ፣ እነዛ እስካሁን ወንበዴዎች እያልክ የምትጠራቸው የያኔ መንፈሰ-ንቁና ቆራጥ የኤርትራ ወጣቶች፣ እነሱ ናቸው ባባቶችህና ባንተ ላይ ያመጹት፡፡ ያው ታሪክ እንደሚመሰክረው ደግሞ፣ ያ ያኔ የታፈነው ነጻነታቸውን፣ ታሪካቸውንና ኤርትራዊ-ባሕራቸውን ብትግልና በዓለማዊ-ህግ ( referendum) ያስመለሱት፡፡ ጓድ ባሕር ሓይል ነበር! ተክልየን አልኩህ! አንተ እንዳልከው ወንበዴዎች አልነበሩም፣ ውንብድናም አይወዱም ፡፡ በባህል፣ በወግና በስነ-ስርአት ያደጉ የኤርትራ ልጆች ናቸው፡፡ ከነዚህም፣ የኤርትራ ባሕርሓይል፣አየርሓይል፣መሃንዲሶች፣ዶክቶሮች፣መምህራኖች ፣ተማሪዎች፣ ገበሬዎች እና ሳይንቲስቶች ይገኙበታል፡፡ ይገርምሃል! ከመንገድ ዳርና ከየ ሻይቤቱ ወይም ከየእርሻ ማሳው ሃይለሰለሴ ወይም ደርግ አላሰባሰባቸውም፡፡ “ኤርትራ ወይ ሞት” ብለው በወለንታቸው ወደ ትግሉ አለም የተቀላቀሉ የኤርትራ ብልጥ-ትውልድ ናቸው፡፡ ባሁኑ ሰአት ደግሞ አንተ እንዳልከው ሳይሆን ፣ ስማቸው “ኤርትራውያን” ነው፡፡ የቀይባሕር ባለቤቶች ደግሞ ናቸው እንዳትረሳው ብየ ነው? የራሳቸው ባንዴራና መንግስት በገዛራሳቸው ተቀዳጅተዋል፡፡ ዓለሙ ብሙሉም፣ እንደ ሃገርና ህዝብ ያከብራቸዋል፡፡ ባንዴራቸው ( የኤርትራ ባንዴራ) ደግሞ፣ በተባበሩት መንግስታት አለማቀፉ ድርጅት ጽሕፈት ቤት ከዓለሟ ጋር ተቀላቅላ ፣ ተንጠልላ ታውለበልባለች፡፡ ይህንን ሃቅ ካልተዋጠልህ ደግሞ በተግባር ለማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ያው ታሪካዊ ሃቁን ፣ በጠባብነትህና ብትምክህተኛነትህ ካልካድከው፣ባሁኑ ሰአት ወደ ይምትናፍቀው ምጽዋ ብትመለስ፣ እነዛ ወንበዴዎች ብለህ የምትጠራቸው የኤርትራ ልጆች /ህዝቦች ብክብርና በደስታ ያስተናግዱሃል፡፡ አይዞህ ! እንዳንተ አይዝቱም፡፡ ይቅር ባዮች ናቸው፡፡ አንተና ግብረአበሮችህ ላደረጋችሁት ታሪካዊ ወንጀል ይቅር ብለውሃል፡፡
ያንተው ወንበዴ ነበር አለም ሃብተ ነጋ
|